¤በአንገቴ ላይ መስቀሉን ከማህተቡ ጋር አስሬ ክርስቶስን እየሰበኩ ምግባሬ እምነቴን ካልገለፀዉ ምኔ ነዉ ክርስቲያን?
¤ክርስቲያን ተብዬ ድራፍት ቤቱን ያጨናነኩት ረቡእ አርብን ሽሬ ስጋ እያማረጥኩ ከተሰለፍኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን?
¤በየመጠጥ ቤቱ በየጭፈራዉ ቦታ 'እሱ ጣጣም የለው...' ተብዬ የምገኘዉ ማህተቤን አሰዳቢ ከሆንኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን??
¤ኦርቶዶክስ እኮ እስክባል ከጫቱ ቅጠል፣ ከትንባሆዉ ጢስ ካልራኩ የድፍረቴ ጥጉ መብቴ እስኪ መስለኝ ቤ/ክ በር ድረስ እያጨስኩ ስደርስ ብቻ ረግጬዉ ከገባው ምኔ ነዉ ክርስቲያን??
¤የከተራዉ የደመራዉ የበአላቱ ቀንነጠላዬን ለብሼ፣/እሱንም በሰበብ/ ስለ ታቦት ብጠየቅ ስለ መስቀል ስጠየቅ መልስ ካልሰጠዉ?
¤የፀሎት መፀሃፍ በአይነቱ መፀሃፍ ቅዱስ በብዛት ደርድሬ ለመግለጥ ግን ከሰነፍኩ..
¤አስቀዳሽ ጿሚ ተብዬ ቅዱስ ስጋዉን ክቡር ደሙን ተቀብዬ ቤቴ ስገባ አንደበቴን ለስድብ ከከፈትኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን??
¤በቅዱስ ቃሉ ማህተብ በስርአተ-ተክሊል ትዳር መስርቼ ሚስቴን ከሰደብኩ፣ከመታው፣ከፈታሁ ምኔ ነዉ ክርስቲያን?
¤ድንግል እናቴን አማላጅ ብዬ ካሉኝ ሁሉ ቀናት ሰንበትን መስጠት አቅቶኝ የእመብርሃንን ታምሯን ካልሰማዉ ምኔ ነዉ ክርስቲያን?
¤ በሃይማኖታዊ በአላት ቅዱሳን በሚከብሩበት ቀን በአለም ሞቅታ ተስቤ ለፆም መያዣ/መፍቻ በሚል ሰበብ ከሰከርኩ፤ከዘሞትኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን?
¤የዝማሬዉ ካሴት ከአለሙ ዘፈን ጋር ደርድሬ ለምርጫ ስቸገር የቅዱሳኑን ስእል ከአለም ሰዎች ጋር ለጥፌ ለመስገድ ስጨነቅ ምኔ ነዉ ክርስቲያን??
¤አገልጋይ ተብዬ ሰ//ት/ቤት ገብቼ በሰከረ አንደበት ለምስጋና ስነሳሳበ በወንዴም በእህቴ ላይ ቂም ይዤ ከወረብኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን??
¤ነጠላ ለብሼ ለመማር ወጥቼ ከሴት/ከወንድ ጋር የቅድስትቤ/ክ አጥር ተደግፌ በሴሰነኝነት ከታወርኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን??
¤እንከን የሌለባት አባቶቼ በጸናት ያቆይዋትቅድስት ቤ/ክ ያስተማረችኝን ካልኖርኩበት ኦርቶዶክስ እኮ ተብዬ ስሟን ካጎደደፍኩ ምኔ ነዉ ክርስቲያን?
0 comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.