የአግዚአብሔር መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ወደአሉበት ወረደ:: የአሳቱን ነበልባልም መታው አሱም አንደነፋስ ቀዘቀዘ የአሳቱም ነበልባል ምን ምን አልነካቸዉም ለመዉታትም አላስቸነካቸዉም:: ያንጊዜም ፫ ሰዎች ስድራቅ ምስሃቅ አብድናጎ በአንድ ቃል አመሰገኑት ባረኩት:: የአባቶቻቺን አምላክ አግዚአብሔር ይባረክ ይመስገን አያሉ:: ስቡህም አሱ ነው ልዑልም አሱ ነው:: ናቡከደነፆርም ሲያመሰግኑ በሰማቸው ጊዜ አደነቀ ፈጥኖ ተነስቶ ቆመና አሺከሮቹን አንዲህ ብሎ ጠየቃቸው አስራቸሁ ከአሳቱ ጉድጉአድ የታላቹሃቸው ፫ ሰዎች አልነበሩም:: ንጉሥ ሆይ አዎን አሉ ንጉሱም አንዲህ አለ አኔ አራት ሰዎች ከአስራት ተፈተው በአሳት መካከል ሲመላለሱ አየሁ የነካቸዉም ነገር የለም:: አራተኛዉም ፊቱ የግዚአብሄር ልጅ ይመስላል:: ከዚህም በኃላ
ናቡከደነፆር ወደምነደው አሳት ጉድጉአድ በር ሄዶ የልዑል አግዚአብሔር አገልጋዮች ስድራቅ ምስሃቅ አብደናጎ ወደዚህ ኑ ዉጡ አለ:: ስድራቅ ምስሃቅ አብድናጎ ከአሳቱ ጉድጉአድ መካከል አፈፍ አፈፍ ብለው ወጡ:: ያን ጊዜም መቁአንንቱ ሹማምንቱ የንጉሡ አለቆች ሁሉ ተሰበሰቡ:: ያን ጊዜም ሰዎቹን አካላቸዉን አሳት አንዳልነካቸው አዩዋቸው የራሳቸዉን ጠጉር አንዳለበለበው የፍታቸዉም መልክ አንዳልጠቆረ የጢስ ሸታ አንኩአን አንደሌለባቸው አዩአቸው:: ናቡከደነጾር ለምድርና ለሰማይ ንጉሥ ለአግዚአብሔር በፊታቸው ሰገደ:: አሁንም የምወዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ አምላካቼን ኤግዚአብሄርን አንለምነው ምንም በፊቱ ብንበድል አሱ በደላችንን ይሰዉራልና ስለ ድካማቸንም ይታገሳልና:: ያለዉን ሁሉ ትወዳለህ ከፈተርከውም ሁሉ ምንም ምን ቸል የምትለው የለም ብሎ መክብብ አንደተናገረ:: ዳግመኛም ሁሉን መፍጠርህና መግዛትህ ሁሉን ይክር አንድጥል ታደርግሃለች ብሎ አንደተናገረ ይህን ሊቀ መላአክት ቅዱስ ገብርኤልን ይልክልን ዘንድ በዚህም በወድአኛዉም ያድነን ዘንድ:: ፫ቱ ወጣቶች ስድራቅ ምስሃቅ አብደናጎን ከምነድ አሳት ጉድጉአድ አንዳዳናቸው ያለትህትና ስራ አይፈፀምምና:: ትህትናስ ስራዉን ሁሉ ለማስፈጸም ምድር ናት ብሎ መጽሐፍ አንደተናገረ ዳግመኛም ለአፋቼን ሐሰት መናገርን አናስለምድ አንዳለ:: ዳዊትም ሐሰት የአመፅ አራስ ነው ብሎ አንደተናገረ ዳግመኛም አቤቱ በጥላህ ስር ማን ያድራል ብሎ መንፈስ ቅዱስን በጠየቀ ጊዜ (ለባልንጀራው) ምሎ የማይከዳ ነው አለ:: በወንጌልም የማይረባ ነገር የሚናገር ሁሉ ይፈረድበታል ተብሎ ተነገረ:: ሁላቸንም በክርስቶስ አደባባይ ፊት አንመርምር ዘንድ አለንና ፀሎቱና በረከቱ አገልጋዩን ይጠብቀው ለዘለዓለሙ አሜን:: ምንጭ ድርሳነ ገብርኤል
0 comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.