የአባታችን የእስትንፋሰ ክርስቶስ የተወለዱበት ቦታ ዳውንት ፀውን ዓባይ ይባላል:: በሰሜን በኩል የእናታቸው ሃገር ደብረ ድባ የቄርሎስ ቦታ ይባላል:: የአባታቸውም ሃገር የእግዚአብሄር አብ ደብር አጠገብ ዳውንት(ደብረአስጋጅ)ይባላል:የአባታቸውምስም መልዓከ ምክሩ ሲባሉ እናታቸው ደግሞ ወለተ ማርያም ይባላሉ:: እነዚህ ባል እና ሚስት በህግ ጸንተው የሚኖሩ እንደ ዘካሪያስ እና እንደ ኤልሳቤጥ መልካም ስራን በመስራት እግዚአብሄርን የሚያገለግሉ ነበሩ:ቀድመውም 2 ልጆችን ወልደው ነበር እና ከዛም እመቤታችንን የተባረከ እግዚአብሄርን የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም ልጅ እንድትሰጣቸው ዘወትር ይለምኗት ነበር:: እግዚአብሄርም ፀሎታቸውን ሰምቶ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ተፀነሱ: ታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ:: ልክ በተወለዱ እለትም ተነስተው በግራቸው ቆመው 3 ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ብለው አመሰገኑ:: 9 ጊዜም ሰገዱ:: ከዚህም በኋላ በ40 ቀናቸው ጥምቀትን ተጠምቀው ስማቸውም እስትንፋሰ ክርስቶስ ተባለ:: ከዚያም ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸው አደጉና አባትየው ዋሻ ውስጥ 60 አመት ወደ ኖረ ቅዱስ ኪራኮስ ወደ ሚባል አባትየአባታችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ረድኤት እና በረከት አይለየን አሜን!!!!!
ምንጭ ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

0 comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.